
ባሕር ዳር: መስከረም 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 2ኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ነገ ሐሙስ ሁለት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።
ቀን 9፡00ሰ ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሦስት ነጥብ ያሳኩ ሲኾን ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን ድሬድዋ ደግሞ ሀምብሪቾ ዱራሜን ማሸነፍቸው ይታወሳል።
ምሽት 12፡00 ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ ።ንግድ ባንክ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከአዳማ ጋር አድርጎ ነጥብ ሲጋራ ሀድያ ሆሳና በበከሉ በመቻል ተሸንፎ ነው የውድድር ዓመቱን የጀመረው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!