የዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ጀመሩ።

38

ባሕር ዳር: መስከረም 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ ፖፕ የመጀመሪያ የሥራ ጉብኝታቸውን በኢትዮጽያ አድርገዋል።

በጉብኝታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ መኾኗ ከድርጅታቸው ዓላማ አንጻር ለላቀ ትብብር ቁልፍ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡

በተፈናቃዮች ላይ የበለጠ መሥራት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጠይቀዋል፡፡

ፍልሰትን በተመለከተ በአካባቢው የሚመለከታቸው ሀገራት የሚኒስትሮች ስብሰባን ለማስተናገድ እየተሠራ መሆኑን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምርት ዘመኑ የተሻለ ግብይት እንዲኖር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next article“ከ200 ብር እስከ 30 ሚሊየን ብር ካፒታል”