አቶ ደመቀ መኮንን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠየቁ።

27

ባሕር ዳር: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠየቁ።

ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢፖፕ ጋር ተወያይተዋል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ ፍልሰትን ለመቆጣጠር ለምታደርገው ጥረት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠይቀዋል።

የዓለም ዓቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ኤሚ ኢ ፖፕ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ጉብኝታቸው ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበልና በማስተናገድ እንዲሁም ተዛማጅ ኹኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ያላትን ዓለም አቀፋዊ ሚና የሚያጎላ እንደኾነም ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን የሥራ ጉብኝት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምክር ቤቱ ብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ሕግ ሆኖ እንዲወጣ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ።
Next articleበኩር ጋዜጣ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ዕትም