ኤደን ሀዛርድ ጫማ ሰቀለ።

103

ባሕር ዳር: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቀድሞው የቸልሲ እና የሪል ማድሪድ የመስመር ተጫዋት የእግር ኳስ ጨዋታ ሩጫውን ማቆሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የ32 ዓመቱ ሀዛርድ እ.ኤ.አ በ2019 ነበር ሪያል ማድሪድን በ89 ሚሊዮን ፓውንድ የተቀላቀለው፡፡

ሀዛርድ በ16 ዓመታት የክለብ ቆይታው ከ700 በላይ ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡ ይህ የእግርኳስ ኮከብ የሚያንቀረቅበው ድንቅ የመስመር ተጫዋች በርካታ ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡

በሪያል ማድሪድ ቆይታው የቻምፒዮንስ ሊግን፣ የዓለም የክለቦች ዋንጫን፣ የኢሮፓ ሱፐር ካፕን፣ ሁለት ጊዜ የላሊጋ ዋንጫን፣ አንድ የኮፖ ዴሲ እንዲሁም ሁለት የስፓኒሽ ሱፐር ካፕን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ስሟል፡፡

ይህ የእግርኳሱ ፈርጥ ኤደን ሀዛርድ እግር ኳስን ለ16 ዓመታት ተጫውቶ ጫማ መስቀሉን ሲናገር “ለዚህ ስኬት እንድበቃ ላደረጉኝ ቤተሰቦቼ ፣ ጓደኞቼ እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቡን አመሠግናለሁ” በማለት ነበር፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ2 ሚሊየን 8 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የወልዲያ ከተማ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
Next article“ግብር ትልቁ የኢኮኖሚ መሰረት እና የክብር ምንጭ ነው” የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሤ