ከ2 ሚሊየን 8 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የወልዲያ ከተማ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

24

ባሕር ዳር: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በወልድያ ከተማ ለሚገኙ 3 ሺህ 2መቶ 64 ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ከ2 ሚሊየን 8 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የከተማዋ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደምሴ አለባቸው ገልጸዋል።

ለተማሪዎቹ 2 ሺህ 9 መቶ 64 ደርዘን ደብተር ፣188 ባኮ እስኪርቢቶ እና ለ253 ተማሪዎች የዩኒፎርም ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል። ድጋፉ ወደ ገንዘብ ሲቀየር ከ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ይገመታል። በወቅቱ የዋጋ ንረት ምክንያት የመማሪያ ቁሳቁስ ገዝተው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች የተደረገ በጎ ተግባር በመኾኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል ኀላፊው።

ድጋፉን የወልዲያ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ፣ ዳሸን ቢራ ፣ ኢትዮ ቴሌኮምና ከንግድ ተቋማት፣ ፣መረዳጃ ማኅበራት ፣ ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣ ከእድሮች በውጭ ከሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የተገኘ ነው መኾኑን ከከተማዉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፍኖተሰላም እና ደብረማርቆስ ከተሞች አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next articleኤደን ሀዛርድ ጫማ ሰቀለ።