“የምጣኔ ሃብቱ ዘርፍ ዋና ምሰሶዎች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

43

አዲስ አበባ: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ብዙ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህል፣ የተፈጥሮ ስጦታዎች፣ አዕዋፍት፣ የዱር አራዊት እና ሊጎበኙ የሚችሉ ድንቅ ሁነቶች አሉን።

እነዚህ ሁሉ ጸጋዎች እንዳሉን ግምት ውስጥ በማስገባት “የምጣኔ ሃብቱ ዘርፍ ዋና ምሰሶዎች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው” ብለዋል።

ዛሬ የተከፈተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች ኢትዮጵያን ምቹ መዳረሻ የሚያደርጋትን በናሙና እንዲያዩ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።

ያለንን አቅም ለማውጣት፣ ኢትዮጵያን የብዙ ውበቶች እና ግኝቶች መዳረሻ አድርጎ ለማስተዋወቅ እና ለማገልገል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራችሁ ያላትን ሀብት ማየት፣ ማውጣት፣ ማስተዋወቅ እና ማገልገል ይጠበቅባችኋል ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምክር ቤቶች የሕዝብ ጥያቄዎችን ለሥራ ኀላፊዎች በማቅረብ ለችግሮች መፍትሔ የማሰጠት ኀላፊነት አለባቸው” የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት
Next articleበተቀመጠ ሕግና ሥርዓት መሠረት ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይገባል ተባለ፡፡