
ባሕር ዳር: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሚሰጡ አስተያየቶችንና ትችቶችን ተቀብሎ ወደ ተግባር መለወጥ ለሥኬት እንደሚያበቃ የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡
የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ መንግሥቱ ቤተ ለአሚኮ እንዳሉት ብዙ ጊዜ ትችቶችን አወንታዊ በኾነ መንገድ ወስዶ መፍትሔ ማዘጋጀት ላይ የሚታዩ ውስንነቶች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክርቤት በመስክ እና በዴስክ የሚያገኛቸውን ምልክታ እና የሕዝብ ጥያቄዎች ለሥራ ኀላፊዎች በማቅረብ ለችግሮች መፍትሔ የማሰጠት ኀላፊነት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
ሕጎች እንዲተገበሩ ማድረግና ኀላፊነትን በሚገባ መወጣት ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መኾኑንም አንስተዋል፡፡
በደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የኔአንተ አለኸኝ አመራርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጎለብት በመኾኑ ከሕዝቡ የሚሰነዘሩ ትችቶችን መውሰድና ለለውጥ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡
እንደ አቶ የኔአንተ ገለጻ ሕዝቡን ከአመራሩ ጋር የሚያገናኙ መድረኮችን ማስፋት ፣ ከመነጋገር ያለፈ ግልጽ የኾነ ሀሳብ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!