የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጸደቀ።

43

ባሕርዳር፡ መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡለትን እቅዶች መርምሮ አጽድቋል፡፡

በጉባዔውም የሕገመንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ፣ የመንግስታት ግንኙነት የዲሞክራሲ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ፣ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴና የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ያቀረቡት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን እቅዶች ካደመጡ በኋላ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበዋል። የየቋሚ ኮሚቴዎቹ አመራሮችም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች በጉባዔው መገኘታቸውንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በ2016 የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት 500 ሺህ ዜጎችን ለመላክ ታቅዷል” የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Next article“ምክር ቤቶች የሕዝብ ጥያቄዎችን ለሥራ ኀላፊዎች በማቅረብ ለችግሮች መፍትሔ የማሰጠት ኀላፊነት አለባቸው” የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት