
ባሕር ዳር: መስከረም 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የሥራ መመሪያን በሚመለከት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል። አሠልጣኞችና የክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካዮችም የአውደ ጥናቱ ተሳታፊ ናቸው ።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ.ር) በቀጣይ ክረምት በሚካሄደው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የምትጠብቀውን ውጤት ለማሰመዝገብ ካሁን በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በማረምና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በቅንጂት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቢልልኝ መቆያ የሥራ መመሪያና የዝግጅት ምዕራፎችን በሚመለከት ለውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ባዘዘው መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!