ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

43

ባሕር ዳር: መስከረም 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች 6ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ የጋራ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ በሀገሪቱ እየተካሄደ ስለሚገኘው የሥራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴ ሪፖርት አቅርበዋል።

በ2015 ዓ.ም ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በተደረገው እንቅስቃሴ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚኾኑ ዜጎች የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መኾናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቷ ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ስለመቻሉም ገልጸዋል። በዚህም 102 ሺህ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ኾነዋል ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት የሀገሪቱ ጠቅላላ የሰብል ምርት ወደ 639 ሚሊዮን ኩንታል እንዲያድግ አስችለናል” ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ
Next article“ለንግግር እና ለሰላም የሚረፍድ ጊዜ የለም” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ