
ባሕርዳር፡ መስከረም 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት በተገኙበት ዛሬ ተከፍቷል።
የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት የፌደራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርእሰ መሥተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!