
ባሕርዳር፡ መስከረም 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚገኙበት ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት በተገኙበት የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይኾናል።
በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የምክር ቤቱ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!