ቅዱስ ጊዬርጊስ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን በድል ጀመረ።

43

ባሕር ዳር: መስከረም 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን ከወልቂጤ ከተማ አድርጎ 4 ለ1 አሸንፏል።

አማኑኤል ኤርቦ፣ አቤል ያለው ፣ተገኑ ተሾመ፣ የወልቂጤ ከተማ ተጫዋች የኾነው ዳንኤል ደምሱ በራሱ ግብ ላይ ለፈረሰኞቹ ግብ አስቆጥረዋል። ስንታየሁ መንግሥቱ ደግሞ ለወልቂጤ ከተማ ብቸኛ ግብን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የአምናውን የሊጉ ዋንጫ ያነሱት ጊዮርጊሶች ዘንድሮ የመጀመሪያውን ጨዋታ በድል ጀምረውታል።

በሊጉ መርሐ ግብር መሰረት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የክልሉ መንግሥት ለሀገር እና ለዜጎች መጠነ ሰፊ ፋይዳ ያላቸውን ኢንቨስተሮች በመሳብ ለሥራ እድል ፈጠራና ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ይሠራል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን
Next article“የግንባታ ዘርፉ የክልሉን ሁለንተናዊ እድገት በማፋጠን በኩል ሚናው አይተኬ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)