በቱርክ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው።

25

ባሕርዳር፡ መስከረም 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቱርክ አንካራ በተካሄደው የሴቶችና የወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡

በወንዶቹ አትሌት ሲሳይ ለማ 1 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡

አትሌት ጪሚድሳ ደበሌ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸናፊ መሆኑንም ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም አትሌት ዘውዲቱ አደራው በሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏም ነው የተሰማው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፋሲል ከነማ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል።
Next article“አፄ ቴዎድሮስ የሚማጸኑበት፣ ሁልጊዜም የሚመኩበት”