
ባሕር ዳር: መስከረም 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪውን ጨዋታ ከሃዋሳ ከነማ ጋር አድርጎ በአቻ ውጤት አጠናቋል።
ዓጼዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተው ነበር።
ከእረፍት መልስ ሃዋሳ ከነማዎች በተከታታይ ሦስት ግቦችን ከመረብ አገናኝተው ፋሲልን 3 ለ 2 መምራትም ችለው ነበር።
በመጨረሻም የዓጼዎቹ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው በጨዋታው ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ደግሞ ከሽንፈት የታደገችውን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው ሦስት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!