
ባሕርዳር፡ መስከረም 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ስምንተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ዛሬ በርከት ያሉ ጨዋታዎችን ሲየያስተናግድ ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ጨዋታዎች ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው በብሬንት ፎረድ 1 ለ 0 በኾነ ውጤት ሲመራ ቆይቶ በባከነ ሰዓት በአስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ሶስት ነጥብ አሳክቷል።
ቸልሲ ከሜዳው ውጭ በርንለይን 4 ለ 1 ሲያሸንፍ ፤ኤቨርተን በርንማውዝን 3 ለ 0 ረቷል።
ፍልሃም ሸፊልድን ፣ቶትንሃም ደግሞ ሉተን አሸንፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!