
ባሕር ዳር: መስከረም 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ኢኳቶርያል ጊኒ ከ ኢትዮጵያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በ9ኛው ደቂቃ እሙሽ ዳንኤል ባስቆጠረቻት ግብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ነበረች። ኾኖም ጊኒዎች ጎል አስቆጥረው አቻ መኾን ችለዋል።
ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአቻቸው ጋር በቀጣይ ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የመክሱን ጨዋታ ያደርጋሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!