የሕገ-መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ከሕገ መንግሥት ትርጉም ጋር በተያያዘ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ምርመራ አካሄደ።

27

ባሕር ዳር: መስከረም 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል እና ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል የውሳኔ ሃሳብ ባቀረበባቸው ጉዳዮች ላይ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

ቋሚ ኮሚቴው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል ያቀረባቸውን ሁለት ጉዳዮች በመመርመርና በመወያየት የቋሚ ኮሚቴው የምርመራ ውጤት የውሳኔ ሃሳብ ተዘጋጅቶላቸው ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ ወስኗል::

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል በሰጣቸው ውሳኔዎች ቅር በመሰኘት በይግባኝ ለምክር ቤቱ የቀረቡ 34 ጉዳዮችን ቋሚ ኮሚቴው በጥልቀት ከመመርመር በኋላ የኮምቴው የምርመራ ውጤት የውሳኔ ሃሳብ ተዘጋጅቶለት ለምክር ቤቱ ጉባኤ እንዲቀርብ ወስኗል::

በመጨረሻም የሕገመንግሥት ትርጉምና የውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየትና መሻሻል የሚገባውን በማሻሻል እቅዱ ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል::

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዛሬ በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ የአርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ይጠበቃል።
Next article“በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በ230 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰሊጥ እየተሰበሰበ ነው” የዞኑ ግብርና መምሪያ