
ባሕር ዳር: መስከረም 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)”የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚኾን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ተማሪዎችም ትክክለኛውን መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ገፆች ላይ እንድከታተሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!