
የኢሬቻ በዓል የገዳ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም መከበሩን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል አስታውቋል፡፡
አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገራችንና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እና ቱሪስቶች የታደሙበት የኢሬቻ በዓል በሰላም እና በልዩ ድምቀት መከበሩን ነው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ያስታወቀው፡፡ የበዓሉ በሰላም መከበር የሀገሪቱን መልካም ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ግብረ-ኃይሉ ጠቅሷል። በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር የድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ ግብረ-ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡