የኢሬቻ በዓልን አብሮነትና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ማክበራቸውን አባ ገዳዎችና የበዓሉ ታዳሚዎች ተናገሩ።

35

የኢሬቻ በዓልን አብሮነትና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ማክበራቸውን አባ ገዳዎችና የበዓሉ ታዳሚዎች ገልጸዋል። ኢሬቻ የፍቅር፣ የአንድነት እና የሰላም ተምሳሌት መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ በዓሉ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበትና መጭው ዘመን የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ፀሎት የሚደረግበት ነው ብለዋል።

አባገዳ አህመድ መሐመድ ኢሬቻ በአብሮነት የሚከበር የወንድማማችነትና ፍቅር መገለጫ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢሬቻ እሴቱን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት። የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በተገኙበት እየተከበረ መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Previous articleየኢትዮጵያን እና አሜሪካን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።
Next articleየኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረኃይል ገለጸ።