
አዲስ አበባ: መስከረም 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የአሜሪካ ሴናተር ማይክ ሮንድሰንንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የአሜሪካ ሴናተር ማይክ ሮንድስን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አፈ ጉባዔ ታገሰ እና ሴናተር ማይክ ሮንድሰን የኢትዮጵያን እና አሜሪካን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል ነው የተባለው። በውይይቱም ስለ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ በስፋት መክረዋል ተብሏል።በቀጣይም ሁለቱ ሀገራትን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!