
ባሕር ዳር: ጥር 24/2012 ዓ.ም (አብመድ) የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ ለመጠየቅ፣ የእገታ ድርጊቱንና የመንግሥትን ዝምታም ለማውገዝ ጎንደር ላይ እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ተማሪዎች ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፡፡
ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ እገታ የተፈጸመባቸው ተማሪዎች የት እንዳሉ፣ ለምን ዓላማ፣ በማንና ለምን እንደታገቱ ደብዛቸው ከጠፋ ሁለት ወራት ተቅጥረዋል፡፡
ፎቶ፡- በኃይሉ ማሞ