
ባሕር ዳር፡ መስከረም 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሁለቱ ምክር ቤቶች 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሰኞ ይካሄዳል።
የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ያቆብ ወልደሰማያት እንደተናገሩት መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምክር ቤቶቹን መከፈት ያበስራሉ።
ሰኞ ከሰዓት በሚኖረው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ፕሬዚዳንቷ የመንግሥትን የበጀት ዓመቱን የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያመላክት ንግግር ለምክር ቤቱ ያደርጋሉ።
በመክፍቻ ሥነ ሥርዓቱ ከምክር ቤቱ አባላት በተጨማሪ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!