
የጎንደር ከተማ አሥተዳድር ነዋሪዎች በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን የእገታ ድርጊት እያወገዙ ነው፡፡
ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ እገታ የተፈጸመባቸው ተማሪዎች ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የጎንደር ከተማ አሥተዳድር ነዋሪዎች እየጠየቁ ነው፡፡
መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ፣ ህግንም እንዲያስከብር ነው በሰላማዊ ሰልፉ እየጠየቁ የሚገኙት፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እያስተላለፏቸው ከሚገኙት መልዕክቶች መካከል ‹‹በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚፈጸምን ግፍ እናወግዛለን፤ የሀሰትና የፈጠራ ታሪኮች ይከልከሉ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ ሚፈጸመው ግፍና በደል በአስቸኳይ ይቁም፤ በዩኒቨርሲቲ የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ በአስቸኳይ ይቁም!›› የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ፎቶ፡- በእመቤት ሁነኛው እና በኃይሉ ማሞ