የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት መሪዎች ቀዳሚ ኾኑ።

47

ባሕር ዳር: መስከረም 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ 100 የአፍሪካ ምርጥ ወጣት መሪዎችን ባወጣው ቾይስዩኤል 100 አፍሪካ ቀዳሚ መኾን ችለዋል።

ቾይስዩኤል 100 አፍሪካ በየዓመቱ በቾይስዩኤል ኢንስቲትዩት ጥናት ተደርጎ በኢኮኖሚ፣ በማኅበረሰብ ነክ እና በባሕል ተፅዕኖ ፈጣሪ የኾኑ 100 ወጣት መሪዎችን ይፋ የሚያደርግ የጥናት ውጤት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቀጣዩ ትውልድ ሀገርን ከነክብሯ እንዲጠብቅ የበኩላችንን ኀላፊነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ የሁመራ ከተማ አረጋውያን ተናገሩ።
Next article“የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ