የዓለም ዋንጫ ዳግም በአፍሪካ ምድር ሊካሄድ ነው።

45

ባሕር ዳር: መስከረም 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2030 እኤአ የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በሦስት አህጉር በሚገኙ ስድስት ሀገራት እንደሚካሄድ የዓለምአቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የዓለም ዋንጫም ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኋላ በአፍሪካ ምድር ለመካሄድ ተቃርቧል።

ሞሮኮ ፣ ፖርቹጋል እና ስፔን የ2030 የዓለም ዋንጫ የማዘጋጀቱን ዕድል ተሰጥቷቸዋል። የዓለም ዋንጫ የተጀመረበትን 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የመጀመርያውን የዓለም ዋንጫ ያስተናገደው አህጉር ላቲን አሜሪካ ሦስት የመክፈቻ ጨዋታዎች ይካሄድበታል። በ1930 እኤአ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ኡራጓይ ተመርጣለች። አርጀንቲና እና ፓራጓይም ሁለቱን የመክፈቻ ጨዋታ ያስተናግዳሉ።ይህንን ተከትሎም ውድድሩ ለመጀመርያ ጊዜ በሦስት አህጉሮች የሚካሄድ ይኾናል።

የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ ፊፋና እግርኳስ እንደተዋሃዱ ነው ብለዋል።

ውሳኔው ረቡዕ በበይነ መረብ በተካሄደው የፊፋ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተወሰነ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት የመጨረሻ ወራት 211 የፊፋ አባላት በሚሰጡት ድምጽ ይፋዊ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ውሳኔም የዓለም አቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ መኾኑም ተነግሯል። ቀደም ብለው ዩክሬንን የዝግጅቱ አካል የማድረግ እቅድ እንደነበራቸውም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አስታወቁ።
Next article“በአዲስ የተደራጀው አመራር የክልሉን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት እየሠራ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ