
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ።
ባሕር ዳር: መስከረም 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎችን እያከናወነ ያለው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ከ ምድብ 5 እስከ 8 የሚካሄዱ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።
የአምናው የዋንጫ ባለቤት ማንቸስተር ሲቲ ወደ ጀርመን ተጉዞ አርቢ ሊፒዚንግን የሚገጥምበት መርሐ ግብር ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል።
ሌላኛው የእንግሊዝ ተወካይ ኒውካስል ዩናይትድ ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ፣ የጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትመንድ ከጣሊያኑ ኤሲ ሚላን የሚያደርጓቸው ጨዋታዎችም ተጠባቂ ናቸው። የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድም የሆላንዱን ፌየኖርድ በሜዳው ያስተናግዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!