
ደብረ ብርሃን፡ መስከረም 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክርቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 39ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አከናውኗል።
በጉባዔው ላይ የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት ለወቅታዊው የሰላም እጦት እና ቀውስ ብልሹ አሠራርና አሉታዊ ተፅዕኖው የገዘፈ ነው ብለዋል።
ተቀዳሚ ከንቲባው በሥነ ምግባር የታነፀ የአገልጋይነት መንፈስ ያለው የሥራ ኀላፊ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው ለ 20 የከተማው የሥራ ኀላፊዎች ሹመት በመስጠት ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡- ዮናስ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!