“ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ከሕዝብ የተሰጠ ኃላፊነትን መወጣት ይገባል” የደብረ ብርሃን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ

43

ደብረ ብርሃን: መስከረም 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አራተኛ ዙር 10ኛ ዓመት 39ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ተካሄዷል።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ መንግሥቱ ቤተ ፤ ምክር ቤቱ በሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ ሥራዎችን ሲሠራ እንደነበር አንስተዋል። ኾኖም ከሕዝቡ የሚነሱ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመገፋፋት እና ምክንያቶችን በመደርደር ሳይመለሱ ቆይተዋል ብለዋል።

ፈፃሚ አካሉ ከሕዝብ የተሰጠ ኃላፊነት በመወጣት የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ለሕዝቡ ፈጣን እና ቀልጣፋ አሠራሮችን ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምክር ቤቱ የቀረቡለትን የአስፈጻሚዎች ሹመት መርምሮ አጽድቋል።

ዘጋቢ፦ ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት የቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ አጸደቀ።
Next article“በዞኑ ከ452 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የእለት ደራሽ ምግብ ይፈልጋሉ” የሰሜን ጎንደር ዞን አሥተዳደር