
ባሕር ዳር: መስከረም 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል።
ጉባኤው በዕለቱ በአስፈጻሚው አካል የቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ በማጽደቅና የ2016 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ በጀት መርምሮ አጽድቋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ ኀይሉ ግርማይ አዳነ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ አሥተዳዳሪ
2. አቶ ፀጋው እሸቴ በምክትል አሥተዳዳሪ ማዕረግ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ መንገድ መምሪያ ኀላፊ
3. ወይዘሮ የሺ ካሴ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ
4. አቶ አብዱረህማን መኮነን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ
5. አቶ አሰፋ ነጋሽ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ጤና መምሪያ ኀላፊ
6. አቶ ገበየሁ ወርቁ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የንግድና ገበያ መምሪያ ኀላፊ
7. ወይዘሮ ትበርህ ታደሰ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሴቶች ፣ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ
8. አቶ እንደሻው ታረቀ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አድርጎ ሹሟል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የ2016 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ በጀት 2 ቢሊዮን 378 ሚሊዮን 993 ሺህ 782 ብር በማድረግ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የተከሰተውን ድርቅ በሰውና እንስሳት ላይ ክፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል የሚቻልበትን አቅጣጫ በማስቀመጥም ጉባኤውን አጠናቅቋል።
ዘጋቢ፡- ሰሎሞን ደሴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!