የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በክልሉ ወቅታዊ ኹኔታዎች ላይ እየተወያዩ ነው።

205

ባሕር ዳር: መስከረም 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች “የሕግ የበላይነት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ” በሚል መሪ መልእክት እየተወያዩ ነው።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በክልሉ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ተፈትቶ ሕዝቡ የሰላም ባለቤት እንዲኾን ለማስቻል ነው ተብሏል።

በውይይት መድረኩ በክልሉ የተሟላ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሲከናወኑ የቆዩ ሥራዎች ተገምግመው የቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአማራ ክልል የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ ለመከላከል በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት ጀምረናል።” ግብርና ሚኒስቴር
Next articleየድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።