ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

68

ባሕር ዳር: መስከረም 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት “ዛሬ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትን አግኝቼ ሥራዎቻቸው ስላሉበት ደረጃ ተወያይተናል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራዊ ምክክሩ በአጨቃጫቂ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት በምናደርገው የጋራ ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አምናለሁ ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
Next article“ስጋት እየኾነ የመጣውን የወባ ስርጭት ለመከላከል የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።” የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት