የሕዳሴ ግድቡን የተመለከተው ድርድር ከታቀደለት ቀን ተራዘመ፡፡

123

ባሕር ዳር፡- ጥር 21/2012ዓ.ም (አብመድ) የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የሦስትዮሽ ውይይት ዛሬም ቀጥሏል፡፡

ኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ በአሜሪካ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት አልተጠናቀቀም፡፡

በአፍሪካ ትልቁ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እንደሚሆን የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በተደጋጋሚ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

ወደ መጠናቀቂያ ደረጃ ላይ እንደሆነ የተነገረለትን ድርድር ለመቋጨት ውይይት ከጀመሩም ሦስት ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ ድርድሩ ትናንት እንደሚጠናቀቅ ነበር የታቀደው፤ ይሁን እንጂ ቢቢሲ አሁን ባወጣው ዘገባ እንደተመላከተው ምክንያቱ ግልጽ ባይደረግም ድርድሩ ዛሬም ቀጥሏል፡፡

ሀገራቱ በአውሮፓውያኑ ጥር 29/2020 ማለትም ትናንት የመጨረሻውን የረቂቅ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ ድርድር ለምን ያክል ጊዜ ሊቀጥል እንደሚችልም ግልጽ መረጃ አልተገኘም፡፡

በኃይሉ ማሞ

Image may contain: sky, mountain and outdoor
Previous articleለማገገም 10 ዓመታት ይወስድበታል ቢባልም በስድስት ወራት የቀድሞ ፀጋውን ተጎናጽፏል፤ የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ!
Next articleኮሮና ቫይረስ የዓለም የጤና ስጋት መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አወጀ፡፡