በላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

42

አዲስ አበባ፡ መስከረም 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፈው እና ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ ማለዳ ሀገሩ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በዓለም የጎዳና ላይ ውድድር በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እና በአንድ ነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን ሁለተኛ ኾኖ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ቡድኑ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኪነ ጥበብ እና ሥነ ጥበብ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ነፊሳ አልመሀዲ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚ አባላት እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዛሬ ከሰዓታት በኋላ በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዕውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት
Next articleየዓለም አቀፍ ቴሌኮም ኅብረት አህጉራዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ።