የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዕውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት

31

አዲስ አበባ፡ መስከረም 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ እውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት።

በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በተስተናገደው የላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

በሁለት ወርቅ፣ በአራት ብር እና በአንድ ነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳልያዎችን የሰበሰበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስካይ ላይት ሆቴል እውቅና እና ሽልማት አበርክቶለታል።

ፌድሬሽኑ በውድድሩ ወርቅ ላመጡ አትሌቶች የ45 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳልያ ላስገኙ የ30 ሺህ ብር፣ ነሐስ ላመጡ ደግሞ የ15 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቷል። ዲፕሎማ ላመጡ አትሌቶች ደግሞ የ10 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

በውድድሩ የተሳተፉ የልዑክ አባላት እና አትሌቶችም እውቅና እና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሸዋ ሮቢት ተሃድሶ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 95 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የተሃድሶ ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት