
ባሕር ዳር: መስከረም 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው በሽዋ ሮቢት ተሃዶሶ ማዕከል በሕግ ጥላ ስር ለሚገኙ 95 ግለሰቦች የመጀመሪያ ዙር የተሃድሶ ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑ ተገልጿል፡፡
የሰሜን ሽዋ ዞን ሥራና ሥልጠና መምሪያ ኀላፊ እና የተሃድሶ ሥልጠናው አስተባባሪ ብርቃብርቅ ተሾመ በዞኑ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ በሽዋ ኮማንድ ፖስት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ግለሰቦች አሉ ብለዋል። እነዚህ ተጠርጣሪዎች በሽዋ ሮቢት ተሃዶሶ ማዕከል ስር እንደሚገኙም ገልጸዋል። ለተጠርጣሪዎች ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ የተሃድሶ ሥልጠና መሰጠት መጀመሩንም አቶ ብርቃብርቅ ተናግረዋል፡፡
የቀጣናው ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ክልከላዎችን በመተላለፍ ወንጀል በሕግ ጥላ ስር የዋሉ ግለሰቦች የተጠረጠሩበትን ወንጀል የማጣራት እና የመለየት ሥራ በመንግሥት እየተከናወነ ነው ብለዋል። የተሃድሶ ሥልጠና ለሚያስፈልጋቸው ግለሰቦችም ሥልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል።
የ104ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሷዲቅ አሕመድ ሠልጣኞች ከተሃድሶው ያገኙትን ክሕሎት በልማት ሥራ ላይ ብቻ ማዋል እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሀርን ሰላም ለመጠበቅም የበኩላቸውን እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
መረጃው የሸዋ ሮቢት ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሸን ጉዳዩች መምሪያ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!