“ትምህርት ቤቶች የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራቸውን ጀምረዋል” የጎንደር ከተማ ሥተዳደር

39

ጎንደር: መስከረም 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅቶቻቸውን አጠናቅቀው የመማር ማስተማር ሥራዎቻቸውን ጀምረዋል።

አሚኮ ቅኝት ባደረገባቸው የቀበሌ 02 አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት እና አዲስ ዓለም አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።

የቀበሌ 02 አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ማሩ አድማሴ ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች ምቹ እንዲኾን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ ተማሪዎቹን መቀበሉን ገልጸዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ዳንኤል ውበት በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የመማር መስተማር ሥራቸውን ጀምረዋል ብለዋል። ተማሪዎችም በየትምህርት ቤቶቻቸው ተገኝተው ትምህርታቸውን ስለመጀመራቸው ተናግረዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጽሐፍ ተደራሽነት ላይ የነበረውን ችግር ከወዲሁ በመፍታት መማሪያ መጽሐፍትን ለተማሪዎች ማሰራጨት መቻሉን ነው ኀላፊው የገለጹት።

በከተማዋ ከ89 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የገለጹት መምሪያው ኀላፊ በተያዘው ሳምንት ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በልዩ ልዩ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎችን የመመዝገቡ ሂደት እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ዘጋቢ፡- ቃልኪዳን ኃይሌ

Previous articleየ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በተሳካ ኹኔታ መጀመሩን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
Next articleበሸዋ ሮቢት ተሃድሶ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 95 ተጠርጣሪ ግለሰቦች የተሃድሶ ሥልጠና እየተሰጠ መኾኑ ተገለጸ።