“ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የትምህርት ቁሳቁስ ለተማሪዎች ድጋፍ ተደርጓል” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ

46

ባሕር ዳር: መስከረም 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የመምሪያው ኀላፊ ዳንኤል ውበት ለ9 ሺህ 647 ተማሪዎች ግምታቸው 14 ሚሊዮን 594 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል። ድጋፉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ ለማድረግ ነው ተብሏል።

ወንድም ካሊፍ ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ፣ ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር ፕሮጀክት ፣ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ፣ ወገን ግብረ ሰናይ ድርጅት እና በእስራኤልና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ የጎንደር ተወላጆች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ድጋፉን ማበርከታቸውን አቶ ዳንኤል ጠቅሰዋል።

አቶ ዳንኤል ከ16 ሺህ በላይ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ አጋዥ መጽሐፍትን በውጭ የሚኖሩ የጎንደር ተወላጆች መላካቸውንም አብራርተዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያጋጥማቸው የነበሩ ችግሮችን እንደሚቀርፍላቸው አስረድተዋል።

የተማሪ ወላጆችም በሰጡት ሀሳብ ድጋፉ የተማሪዎችን ማቋረጥ ይቀንሳል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ አገኘሁ አበባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአንድ ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ።
Next article“የተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መኾን መሠረት ይጥላሉ።” አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ