በላቲቪያ ሪጋ የሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ዛሬ ይጀመራል።

38

ባሕር ዳር፡ መስከረም 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በሰባት ሴት እና በስድስት ወንድ ተጠባቂ አትሌቶች የምትሳተፍበት የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት ይጀመራል፡፡ በሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ኢትዮጵያን ይወክላሉ። ውድድሩም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 5፡50 ላይ ይደረጋል፡፡

በዚሁ ርቀት 12፡15 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጐስ ገብረ ሕይወት የሚሳተፉ ይኾናል፡፡ 7፡00 ላይ በ1 ማይል ርቀት በሚከናወነው የሴቶች ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ይሳተፋሉ። በተመሳሳይ ርቀት 7:10 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ታደሰ ለሚ ይሳተፋል፡፡

7፡30 ላይ በሚደረገው የሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ጽጌ ገብረ ሰላማ፣ ያለምጌጥ ያረጋል እና ፍታው ዘርዬ ይሳተፋሉ፡፡ በዚሁ ርቀት 8:15 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ጀማል ይመር፣ ንብረት መላክ እና ፀጋዬ ኪዳኑ እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ64 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ማከናወኑን የደቡብ ወሎ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next articleበሪጋ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።