
ባሕር ዳር፡- ጥር 20/2012ዓ.ም (አብመድ) ቻይና በኮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያስችል ሆስፒታል በ48 ሰዓታት ገንብታ ሥራ አስጀምራለች፡፡
በቻይናዋ ሁቤ ክፍለ ግዛት ውሃን ከተማ ገዳዩ ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ እስካሁን 132 ቻይናውያን ለህልፈት ሲዳረጉ በዓለማችን በሽታው በተከሰተባቸው ሀገራት 6 ሽህ ሰዎች መታመማቸውን የዓለም የጤና ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡
በበሽታው የያዙ ሰዎችን ለማከም ያስችለኛል ያለችውን ባለ 1 ሺህ የህሙማን አልጋዎች ሆስፒታል ቻይና በሁዋንጋንግ ከተማ በሁለት ቀናት አስገንብታ ሥራ አስጀምራለች፡፡
ሥራውን በ48 ሰዓታት ለማጠናቀቅ ከ500 በላይ ሠራተኞች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ ሀገሪቱ ተጨማሪ ሆስፒታሎችን እንደምትገነባም ነው የተዘገበው፡፡
ምንጭ፡- ዴይሊ ሜል
በአስማማው በቀለ