
ባሕር ዳር: መስከረም 20/2016 (አሚኮ) ባሕር ዳር ከተማ በ2023/24 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ ጋር ያደርጋል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ 60 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ሃማዲ አግሬቢ ኦሊምፒክ ስታዲየም ይከናወናል።ክለቦቹ መስከረም 6/2016 በአበበ ብቄላ ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ በሀብታሙ ታደሰ ግቦች ባሕር ዳር ከነማ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባቱን ያረጋግጣል። የጣና ሞገዶቹ በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ የታንዛንያውን አዛም ክለብ በደርሶ መልስ አሸንፈው እዚህ መድረሳቸው ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!