ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ሰዎች የኮሌራ መከላከያ ክትባት ተሰጠ

49

ባሕር ዳር: መስከረም 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮሌራ በሽታን ለመከላከል በተካሄደ የክትባት ዘመቻ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች መከተባቸውን የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል ከመስከረም 5/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞችን ጨምሮ ተጋላጭ በሆኑ ዘጠኝ ወረዳዎች ክትባቱ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አብርሃም አምሳሉ ኮሌራን ለመከላከል ክትባት አንዱ መንገድ ነው ብለዋል፡፡ ነገር ግን የበሽታው ብቸኛ የመከላከያ መንገድ ስላልሆነ ኅብረተሰቡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ሊጠብቅ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተዘራው አልበቀለም፣ በማሳው ልምላሜ አልታየም”
Next articleሻሸ እና ጓደኞቿ የበጎ አድራጎት ማኅበር ለ2 መቶ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ