በሰሀላ ሰየምት ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ46 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

39

ባሕርዳር፡ መስከረም 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰሀላ ሰየምት ወረዳ በተከሰተው ድርቅ ከ46 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ጥቂት እውነታዎች፦

👉ሰሀላ ሰየምት ወረዳ 13 ቀበሌዎችን የያዘ ነው።
👉ወረዳው የ2015/2016 ዓ.ም የምርት ዘመን ድርቅ ተከስቶበታል።
👉ወረዳው ከፊል አርብቶ አድር ነው።
👉ወረዳው መደበኛ ዝናብ በሚያገኝበት ወቅት መጠነኛ ሰብል ይመረት ነበር።
👉የወረዳው አርሶ አደር በስፋት ኑሮውን የሚገፋው በእንስሳቱ ነው።
👉በወረዳው 104 ሺህ 430 የጋማ ከብት፣ 22 ሺህ 121 በግ እና ፍየል ይገኝበት ነበር።

የነዋሪዎች ሁኔታ፦

👉 ከ46 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
👉በወረዳው እንዲህ አይነት ድርቅ ተከስቶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ወረዳው በዚህ ወቅት የሚገኝበት እውነታ፦
👉396 ሺህ 760 እንስሳት ለከፋ ድርቅ ተጋልጠዋል።
👉116 ሺህ 900 እንስሳት ወደ አጎራባች ዞን ተሰደዋል።
👉እስካሁን 2 ሺህ 457 እንስሳት በድርቅ ምክንያት ሞተዋል።
👉ለእንስሳቱ ምንም አይነት መኖ የለም።

ድርቁ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል የሰሊጥ ሰብል እየተሰበሰበ ነው።
Next article“ውሻን በወቅቱ በማስከተብ ውሻን የሚያሳብድ በሽታን መከላከል ይገባል” የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት