ኢጋድ በኬንያ ሞያሌ የድንበር ተሻጋሪ ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስመረቀ።

52

ባሕርዳር፡ መስከረም 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢጋድ በኬንያ በኩል በምትገኘው ሞያሌ ከተማ የድንበር ተሻጋሪ ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስመርቋል። ቢሮው በኬንያ መንግሥት በኩል ለኢጋድ ተላልፏል።

ከኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ የተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች እንዲሁም በሞያሌና መርሳቢት ከሚገኙ ማኅበረሰቦች የተውጣጡ ተሳታፊዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል። ጽሕፈት ቤቱ በኢትዮጵያና ኬንያ የሚገኙ ድንበር ተሻጋሪ ማኅበረሰቦችን የበለጠ ለማግባባትና በትብብር ለመስራት እንዲሁም ህገወጥ ስደትን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም ተገልጿል።በተለይም በአካባቢው ለሚኖረው ማኅበረሰብና ስደተኞች ማህበራዊ አገልግሎቶችንና መሰረተ ልማትን ለማድረስ አቅም ይፈጥራል ነው የተባለው።

ኢቢሲ እንደዘገበው ጽሕፈት ቤቱ የተቋቋመው የጋራ እቅድን በማውጣትና መረጃን በመለዋወጥ፣ የህዝቡን ድንበር ተሻጋሪ የንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በማመቻቸት፣ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን በማጣጣም ክልላዊ ውህደትን ለማፋጠን ነው ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አዲስ የአመራር ምደባ ተደረገ።
Next articleተቋማቱ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።