
ባሕርዳር፡ መስከረም 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወቅታዊ ኹኔታን በጥልቀት በመገምገም ወቅቱን የሚመጥን ከክልል እስከታች ሪፎርም እና ስምሪት እየተሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት፦
1)አቶ አብደላ አህመድ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
2)አቶ አሊ መሀመድ በሽር የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊና የኦሮሞ ብ/ዞን ምክትል አስተዳዳሪ
3)አቶ አህመድ መሀመድ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት/ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
4) አቶ የሱፍ እንድሪስ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር መንገድ መምሪያ ኃላፊ
5) አቶ አህመድ ሀሰን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሲቪልሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ
6)አቶ መሀመድ ይማም የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
7)አቶ መሀመድ መኮንን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ንግድና ገበያ መምሪያ ኃላፊ
8) አቶ አህመድ እብራሂም የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ
9)ወ/ሮ አንሻ እንድሪስ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር መስኖና ቆላማ አካባቢዎች መምሪያ ኃላፊ
10)አቶ ሳዳም ሁሴን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ወጣትና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ በመኾን ተሹመዋል።
ስምንት የብሔረሰብ አሥተዳደር ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎችም እንደተደራጁ ተጠቅሷል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ አህመድ እንደገለፁት ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ አመራር የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
የአደረጃጀቱ አላማ በዋናነት አሁን እንደ ክልል እና እንደ ብሔረሰብ አሥተዳደር እየገጠሙን ያሉ ፈተናዎችን ለመሻገር የሚያስችል መዋቅር በማደራጀት የተጀመረውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ተግባራት የበለጠ በማጠናከር ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!