
ባሕር ዳር፡ መስከረም 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ አሸናፊው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የ2023/24 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከግብጹ አል አህሊ ጋር ዛሬ ያከናውናል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ 75 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ክለቦቹ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አል አህሊ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት ተጋጣሚውን ከሦስት ግብ በላይ ልዩነት በላይ ማሸነፍ ይኖርበታል።
ማሊያዊው አልቢተር ቡቡ ታሪ የሁለቱን ክለቦች የመልስ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
አል አህሊ የባለፈው ውድድር ዓመት የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!