ለማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ አቀባበል ተደረገላት።

48

ባሕር ዳር: መስከረም 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ያሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ አቀባበል ተደርጎላታል።

አትሌት ትዕግስት አሰፋ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የበባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውላታል።

በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል።

በ49ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2 ስዓት 11 ደቂቃ 53 ሰከንድ በሆነ ጌዜ ውድድሩን በመጨረስ የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን መስበሯ ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጃዊ በፊፊ መስቀልን ታደምቃለች፤ እርቅ አውርዳ ግጭትን ታርቃለች”
Next articleጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በካይሮ ያደርጋል