
ባሕር ዳር: መስከረም 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ልክ የዛሬ ዓመት በድንገት ሕይወቱ ያለፈው የዝነኛው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው::
ዛሬ ማለዳ የድምፃዊው ቤተሰቦች፣ የሙያ አጋሮች እና አድናቂዎች በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የማዲንጎ ሐውልት ተመርቋል::
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ቆይታ ያደረገው የማዲንጎ የሙያ ባልደረባ አርቲስት ብርሀኑ ተዘራ በቀጣይ በድምፃዊው ተጀምረው የተጠናቀቁ የሙዚቃ ሥራዎች ለአድማጭ እንደሚቀርቡ ገልጿል::
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!