“የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጎ እየተሠራ ነው” የቱሪዝም ሚኒስቴር

43

ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያውያን ዘንድ ልዩ ቦታ ከሚሰጣቸው ወራቶች ውስጥ የመስከረም ወር አንዱ ነው፡፡ የዘመን መለወጫ ዕንቁጣጣሽ፣ የመስቀል ደመራ፣ ያሆዴ መስቀላ፣ ዮ ማስቃላ፣ ጊፋታና እሬቻ በመስከረም ወር ብቻ የሚከበሩ በዓላት ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የመስከረም ወር በርካታ የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት ወር ነው። በዓላቱ አብሮነትን በማጠናከርና ሕዝብን በማቀራረብ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ሲሆን ጎብኝዎችን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። ይህንን ወቅት ተከትሎ በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን በማስመልከት የቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ነጋሽን ማብራሪያ ሰጥተዋ።

ሚኒስቴሩ የሀገሪቱን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለጎብኝዎች በስፋት ሲያስተዋውቅ መቆየቱን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። የክልል ቱሪዝም ቢሮዎችም መሰል ሥራዎችን ማከናወናቸውን ገልጸዋል። ጎን ለጎንም ለበዓላቶቹ ለሚመጡ የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅና ቆይታቸውን የሰመረ ለማድረግ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አሳውዋል።

ጎብኝዎች ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ከአቀባበል ጀምሮ እየተሠራ መሆኑን ገልጸው አስፈላጊ መረጃዎችን የሚያሳውቅ የጎብኝዎች መረጃ ማዕከል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ከመሥተንግዶ ጋር በተያያዘ እክል እንዳይገጥማቸው ከሆቴሎች እና ከአስጎብኝ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመስቀል ደመራ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው።
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo: Fulbaana 15/2016